1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቅሬታ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ዓርብ፣ የካቲት 6 2012

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቀደም ሲል ዩኒቭርሲቲው ያደርግ የነበረውን የገንዘብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማቋረጡ ትምህርታቸውን ባግባቡ ለመማር መቸገራቸውን ተናገሩ። በተለይ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ገንዘብ አግኝተው ትምህርታቸውን ለመቀጠል በማይፈልጉት ሥራ ጭምር እየተሰማሩ አንደሆነ አመልክተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3Xn0R
Äthiopien Bahir Dar | Studenten mit Sehbehinderung
ምስል DW/A. Mekonnen

አካል ጉዳተኞች ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ተቸግረዋል

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትናንት ተሰባስበው ሰላማዊ ሰልፍ ይዘት ባለው መልኩ ቅሬታቸውን በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ህንፃ በመገኘት መፈክሮችን በማሰማት ነው ዩኒቨርሲቲው ጥያቄያችን አንዲመልስላቸው የጠየቁት፡፡

የ2ኛ ዲግሪውን በፖለቲካል ሳይንስ በባሀር ዳር ዩኒቨርሲቲ እየተከታተለ ያለው ኤፍሬም መንገሻ የሰልፉን ዓላማ ዶይቼ ቬለ አብራርቷል፡፡  ኤፍሬም አንደሚለው ለአካል ጉዳተኛ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ያልተሟሉ በመሆኑ በግቢ ውስጥ ለመንቀሳቀስም ሆነ ለማጥናት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

አጅግአየሁ ተክለዮሐንሰ የኛ ዓማት የቋንቋ ተማሪ ሰትሆን የኤፍሬምን ሀሳብ ትጋራላች፣ “ቁሳቁሶችን በብድር ግዙና አንደከዚህ በፊቱ ዩኒቨርሲቲው ይክፍካችኋል ቢባልም ዩኒቨርሲቲው መልሶ ሊከፍል ፈቃደኛ አልሆነም” ብላለች።

የ2ኛ ዓመት የቋንቋ ተማሪ አበራ አሰፋ አንዳለው ዩኒቨርሲቲው በየወሩ ለማንበቢያና ለንፅህና መጠበቂያ እስከ 1000 ብር፣ እንዲሁም ለተለያ ወጪዎች ደግሞ በዓመት እስከ 8000 ብር ወጪ ያደርግ አንደነበር ጠቀሶ አሁን ግን ያ ሁሉ ቀርቶ በወር 250 ብር ብቻ አንደሚሰጣቸው አስድቷል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ አራጋው ብዙዓለም ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ “ቀደም ሲል ይከፈል የነበረው የትምህርት ቁሳቁስ ማሟያ የተቀነሰው ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማ ትብብ ሚኒሰትር በወረደ ደብዳቤ ነው፡፡ ሆኖም የተማሪዎቹን ጥያቄ ተቀብለን ክፍያው እንዲሻሻል ከፌደራልም ሆነ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሩ ጋር እየመከርን ነው” ብለዋል፡፡

በባህርዳር ዩኒቭሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮችና ደረጃዎች የሚማሩ 110 አይነስውራንና ሌሎች የተለያየ ጉዳት ያለባቸው 13 ተማሪዎች እንደሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የአካል ጉዳተኞች ማህበር ሰብሳቢ ተማሪ እጅግዓየሁ ተክለዮሐንስ ገልፃለች፡፡

ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ