የአቡነ ማቲያስ የአዲስ ዓመት መግለጫ
ዓርብ፣ ጳጉሜን 2 2010ማስታወቂያ
ለኢትዮጵያ አንድነት የሚበጀው እግዚአብሔርን እና ህዝቡን ማዕከል አድርጎ መሥራት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ተናገሩ ። አቡነ ማትያስ ዛሬ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ህዝቡ ከምንም በላይ ለፍቅር እና ለአንድነት ቦታ እንዲሰጥ ተማጽነዋል። በሀገሪቱ የሚካሄደው ለውጥ እንዳይሰናል ህብረተሰቡ በመጪው ዓመት መቃቃር እና ጥላቻን ከሚያስከትሉ አባባሎችም እንዲርቅም ጠይቀዋል። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ