የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳት እና አስተያየት
ረቡዕ፣ ነሐሴ 3 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት ደንግጎት የነበረዉን የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳቱ በሐገሪቱ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰዉን በደል እንደማያስቆመዉ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን አስታወቁ።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ያነጋገራቸዉ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉት አዋጁ ተነሳም-አልተነሳ ሰዎች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታሰራቸዉ፤መንገላታታቸዉ እናና ቤታቸዉ መፈተሹ አይቆምም።መንግሥት አዋጁን ያነሳዉ ምዕራባዉያን መንግስታትን ለማስደሰት ነዉ ያሉም አሉ።የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈዉ አርብ ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ለአስር ወር የፀናዉ አዋጅ ነገ በይፋ ይነሳል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ