አዋጁ ማሻሻያ
ረቡዕ፣ መጋቢት 6 2009ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ዛሬ አስታወቀ ። የኮማንድ ፖስቱ ሃላፊ እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዛሬ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ በኤኮኖሚ አውታሮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል ተብሎ የተጣለው ሰዓት እላፊ መነሳቱን ተናግረዋል ። ከዚህ ሌላ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል ፣ ብርበራ ማድረግ እና ንብረት መያዝ በተሻሻለው መመሪያ እንዲቀር መደረጉንም ሚኒስትሩ አስታውቃዋል ። ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ከተነሱት እገዳዎች ውስጥ በራድዮ በቴሌቪዥን በጽሁፍ በፎቶግራፍ ቲያትር እና ፊልም የሚተላለፉ መልዕክቶች ላይ የተጣለው እገዳ ይገኝበታል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ