የአምዓቱ የልማት ግብና አፈፃፀሙ13 መስከረም 2003ሐሙስ፣ መስከረም 13 2003የተመድ ከአስርት ዓመታት በፊት የቀረፀዉን የአምዓቱን የልማት ግብ አፈፃፀም ለመገምገም ለሶስት ቀናት በድርጅቱ ጽህፈት ቤት ኒዉዮርክ የተካሄደዉ ጉባኤ ተጠናቋል።https://p.dw.com/p/PL50...የልማት ግቦቹ አመላካቾች በዛፎቹ መካከል ...ምስል DWማስታወቂያ በጉባኤ የተገኙት አባል አገራት ያቀረቡትን ዘገባና የሰነዘሩትን ሃሳብ ተመርኩዘዉም የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ባን ጊ ሙን ቀሪዎቹ አምስት ዓመታት እቅዱ የሚሳካበት ይሆናል የሚል ተስፋ ያዘለ የማጠቃለያ ሃሳብ ሰንዝረዋል። ያ ማለት ግን አሁንም ከታሰበዉ ለመድረስ የሚያደናቅፉ ችግሮች የሉም ማለት እንዳልሆነም ተጠቁሟል። ክርስቲና ቤርግማን፤ ሸዋዬ ለገሠ፤ ሂሩት መለሠ