1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ጦርነት - የፓርላማ አባሎች እና የአዲስ አበባዉ በማንነት ላይ ያተኮረዉ እስር

ዓርብ፣ ነሐሴ 5 2015

የአማራ ክልል ጦርነት - የፓርላማ አባሎችን ጨምሮ በአዲስ አበባ በማንነት ላይ ያተኮረዉ እስር ፤ በፖሊስ ቁጥጥር ስር - የጅምላ እስር። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመላ ሃገሪቱ የሚታዩ ግጭቶች “ያላንዳች ቅደመ ሁኔታ ቆመው” “በአስቸኳይ” በምክክር እንዲፈቱ ጥሪ ማቅረቡ በተሰኙ ርዕሶች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች ተካተዋል።

https://p.dw.com/p/4V58x
Social Media Apps | WhatsApp Facebook Twitter Instagram
ምስል Nasir Kachroo/ZUMA Press/imago images

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

የአማራ ክልል ጦርነት - የፓርላማ አባሎችን ጨምሮ በአዲስ አበባ በማንነት ላይ ያተኮረዉ እስር፤ የሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥሪ፤ እንዲሁም በትግራይ የረሀብ አደጋ የተሰኙ ርዕሶች ተቃኝተዋል

የአማራ ክልል ጦርነት - የፓርላማ አባሎችን ጨምሮ በአዲስ አበባ በማንነት ላይ ያተኮረዉ እስር ፤ በፖሊስ ቁጥጥር ስር - የጅምላ እስር። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመላ ሃገሪቱ የሚታዩ ግጭቶች “ያላንዳች ቅደመ ሁኔታ ቆመው” “በአስቸኳይ” በምክክር እንዲፈቱ ጥሪ ማቅረቡ ፤ ብሎም በአማራ ክልል ያለው ግጭት እና አለመረጋጋት፤ “በከፍተኛ ጥንቃቄ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት” ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥሪ ማቅረባቸዉ፤ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ስለ አማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ስለሀገሪቱ አለመረጋጋት እንዲሁም ”በትግራይ የምግብ እርዳታ ከተቋረጠ ወዲህ 1411 ሰዎች በረሃብ ሞተዋል” ሲል የትግራይ አስተዳደር መግለፁ በተሰኙ ርዕሶች ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን ጨምቀን ይዘናል።

Äthiopien Kommunikationsbüro der Amhara Region
የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ምስል Alemnew Mekonnen

ናስር ይልማ የተባሉ አላህ  ፈጣሪችን ሆይ ሀገራችንን ሰላም አድርግልን ሲሉ ለአምላካቸዉ ተማጽኖ አቅርበዋል።  ስርሶ ፏፏተ የተባለ ስም ያላቸዉ ሌላዉ አስተያየት ሰጭ  ”ጦርነቱን ይላሉ ጦርነቱን  በሁለት አቅጣጫ ማየት ያስፈልጋል ። ፌደራል መንግስት ጋር የሚታየው ችግር እንደ ነበረ ሆኖ፤  ሁል ግዜ ጦርነት የሚሰብኩ ግለሰቦችን ደግሞ ማየት አስፈላጊ ነዉ። የኢትዮጵያን መንግሥት  በፕሮፖጋንዳ አሳስተው ነው ወደ ያልተፈለገው ግጭት ውስጥ ያስገቡን አካላት ይህን ሥራቸዉን ሊያቆሙ ይገባል እላለሁ” ብለዋል። 

አፋን ሙሳ ኡስማን፤ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ፤ ”ኢትዮጵያዊ ሁሉም አማራ ክልልን ከችግር ማዉጣት ይጠበቅበታል። አብሮ መጫወት እና መስራት አለበት። ይህ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያለው ክልል ሰላም ሊያገኝ ይገባዋል። ሰላም ለሀገራችን ሰላም ለሁላችንም ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።”

ገመቹ ሻሌ ኦጋቶ፤ የተባሉ የማኅበራዊ መገናና ዘዴዎች ተጠቃሚ፤ ”በጣም አዝኛለሁ ይላሉ። በጣም አዝኛለሁ  ለተጎጂዎች በሰማል ጤናችሁን ይመልስላችሁ። ለሟች ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ ልባዊ መፅናናትን እመኛለሁ። ሰላም ለኢትዮጵያ!” ብለዋል።

ኤርሚ ጆክ የተባሉ እና በርካታ አስተያየት ሰጭዎች፤ ድል ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ሲሉ ነዉ አስተያየት ያስቀመጠዋል። ፋንታስቲክ ቲም የተባሉ እና ሌሎች በርካቶች ደግሞ ድል ለፋኖ ሲሉ በፊስቡክ አስተያየታቸዉን ጽፈዋል።

አማረ ላቭ የተባሉ አስተያየት ሰጭ ፤ የታሰሩትን የፓርላማ አባላትን በማስመልከት፤ ”ጀግናን በማሰር የሚመጣ ለውጥ የለም። የታሰሩት የፓርላማ አባላት የህዝብ አለኝታዎች ናቸው። መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊለቃቸዉ ይገባል” ብለዋል።

Symbolbild Indien Twitter
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅንት ምስል Diptendu Dutta/AFP

ናትናኤል ታመነ በበኩላቸዉ፤ ህዝብ የመረጠውን ማሰር ህዝብን መናቅ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ትቅደም ፤ ብሔርተኛና ፅንፈኛ ይውደም ፤ ያሉት ደግሞ አሰፋ ኢቢሳ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ናቸዉ።

ታምራት ዳንኤል የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚ፤” ጦርነት አይነሳ እንጂ ከተጀመረ ሁሉንም ይጎዳል። አሁን ሁላችንም በከፍተኛዉ ተጎድተናል። ችግሩ ካለፈው አለመማራችን እና እኔ ብቻ ባይነት እያጠፋን ነው” ሲሉ አስተያየታቸዉን ቋጭተዋል።

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት“አልፋ ሚዲያ” የተሰኘው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን መስራች እና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፤ የሁለተኛ ዲግሪ ምርቃቱን ከተካፈለ በኋላ በ መኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉ፤ አሳፋሪ ነዉ። መንግሥት በማንነታቸዉ ያሰራቸዉን አማሮች በሙሉ በአስቸኳይ ሊፈታ ይገባል ሲሉ አስተያየት የጻፉት አበበ ማሩ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ናቸዉ። 

ሰላም ዶቼ ቬለዎች ያሉን ደግሞ አህመድ በየነ ናቸዉ። ”ሰላም በሰማይ ላይ እንዳለች ላም ወተትዋ ባልዲ ባይሞላም ሰላም ብለናል ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለአማራ ክልል” ብለዋል።

Uganda | Smartphone Nutzer in Kampala
የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በአፍሪቃ ምስል YASUYOSHI CHIBA/AFP/Getty Images

በሽር ኢድሪስ የተባሉ አስተያየት ሰጭ፤ "ብዙዎች ሀገርን ትልቅ ለማድረግ ሲሉ እራሳቸውን አሳንሰዋል። ሌሎች ደግሞ እራሳቸውን ትልቅ ለማድረግ ብለው ሀገራቸውን አሳንሰዋል"። ባልበሰለና ባልበለፀገ አዕምሮ ሀገርን መምራት ሀገርን ከአለት ጋር ከማላተም ውጪ ሌላ ውጤት አያመጣም። በሀገራችን  ላይ የሚገኙ የተለያዩ እምነቶች ፣ ሕዝባዊ እሴቶች ፣ ማህበረሠባዊ ግንኙነቶች ፣ የህዝብ የርስ በርስ ነባር ትስስር ፣ ሀገራዊ ሉዓላዊነትንና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እየተሸረሸረ ነው” ሲሉ ጽፈዋል።

ብሩክ ማሞ በራካ የተባሉ ደግሞ እንዲሂ ይላሉ፤ ”የኢትዮጵያውያን ጥያቄ የኢትዮጵያን ችግር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ በውይይት መልስ ማግኘት አንድ እና ብቸኛዉ መፍትሄ ነዉ” ሲሉ በቃል አጋኖ አስተያየታቸዉን አብቅተዋል።

ስለኒጀር የምንግሥት ግልበጣ ስንዘግብ የሰሙ መላኩ ኢድሪስ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ በበኩላቸዉ፤ የራስዋ አሮባት አሉ ሲሉ ሽሙጥ ቢጤ አስተያየት ጣል አድርገዉልናል።

በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመላው ሀገሪቱ የሚታዩ ግጭቶች “ያላንዳች ቅደመ ሁኔታ ቆመው” “በአስቸኳይ” በምክክር እንዲፈቱ ጥሪ ሲል  አቅርቧል። ኮሚሽኑ ባለድርሻ አካላትን “በማቀራረብ፣ የልዩነት አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለማወያየት እና ለመመካከር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑንም” አስታውቋል።የዐቢይ የፓርላማ ዉሎ፤ የቀጠለዉ አፈናና ግድያ፤ በትግራይ በረሃብ ሰዎች እየሞቱ ነዉ መባሉ

ሰዉነት ተሰማ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ፤ ቢዘገይም አሁንም አልረፈደም። እባካችሁ በዉይይት ችግሮችን መፍታት ስልጣኔ ነዉ። እንወያይ ብለዋል። እሳ በሽር እሳ የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚ፤ ” ይህ ኮሚሽን ይህ ኮሚሽን እኮ ስራ ሳይሰራ የፈረሰ ኮሚሽን ነው”ብለዋል። 

”ዝም ብሎ ፉከራ ይብቃ” የሚሉት ደግሞ ፋሲል ቸኮል ናቸዉ። ”ዝም ብሎ ፉከራ ይብቃ። ለሰላም ቅድሚያ መስጠት ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል” ሲሉ አስተያየታቸዉን ደምድመዋል። ደጀኔ ዘዉዴ አደብ ግዙ ሲሉ አስተያየታቸዉን ይጀምራሉ። ”ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ነው ። እናም ምላሳቸውን የሚያስረዝሙትን ጠብ የሚዘሩትን አደብ ግዙ ሊባሉ ይገባል”ብለዋል።  የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ከተቋረጠ ወዲህ ባለው ግዜ ብቻ በትግራይ 1411 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሞተዋል ሲል  የክልሉ አስተዳደር አስታወቋል።  በእርዳታ የሚቀርብ ምግብ ላልተፈለገ ዓላማ ውሏል በሚል ምክንያት ከአምስት ወራት በፊት ዓለም አቀፍ ለጋሾች የምግብ ርዳታ አቅርቦት ለትግራይ ክልል ቀጥሎም ለመላዉ ሀገሪቱ ያቋረጡ ሲሆን ይህ እርምጃ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ መፍጠሩን የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በዚሁ ሰሞን አስታውቋል።

Tigray Flüchtlingscamp Eritrea
በትግራይ ክልል በረሃብ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር እየጨመረ ነዉምስል Million Haileselassie /DW

በዚህ ዘመን ”ሰዎች በረሃብ መሞት የለባቸዉም” ሲሉ አስተያየት የጻፉት አዲስ አበበ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ናቸዉ።

ደበላ ኪታ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ፤ ”ለእርዳታ የተላከውን ስንዴ ተሰርቆ እርዳታ በመቆሙ ይህን ያህል ሰዉ በረሃብ መሞቱን መስማት የሚያሳዝን ነዉ፤ ውርደትም ነው” ብለዋል። እየሩሳሌም ቅጣዉ የተባሉ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚ፤ ”ይህ ችግር ሳይባባስ መንግሥት በትግራይ በረሃብ ለተጎዱት ሊደርስ ይገባል። የዉጭ ሃገር ለጋሾች የሚሰጡት የእርዳታ እህል እንዳይሰረቅ ሊጠብቅም ሃላፊነት አለበት” ሲሉ አስተያየታቸዉን ቋጭተዋል።

ሙሉዉን ጥንቅር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ