1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ የዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ውሎ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 30 2015

በአማራ ክልል በተለይ በምዕራብ ጎጃም ዞን ከሰሞኑ በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሲደረጉ የነበሩ ውግያዎች ዛሬም በከባድ መሳሪያ ታግዘው ተጠናክረው መቀጠላቸውን የየአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዞኑ ውግያው ተጠናክሮ ከቀጠለባቸው አካባቢዎች መካከል አራፋት ፣ ገንዳ ዉሃ እና ዝኩል ቃና የተባሉ አካባቢዎች ተጠቃሾች ናቸው ።

https://p.dw.com/p/4Vz0g
Äthiopien | Kämpfer der Fano-Miliz in Lalibela in der nördlichen Amhara-Region
ምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ዛሬም ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል

በአማራ ክልል በተለይ በምዕራብ ጎጃም ዞን  ከሰሞኑ በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሲደረጉ የነበሩ ውግያዎች ዛሬም በከባድ መሳሪያ ታግዘው ተጠናክረው መቀጠላቸውን የየአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዞኑ ውግያው ዛሬም ተጠናክሮ ከቀጠለባቸው አካባቢዎች መካከል አራፋት ፣  ገንዳ ዉሃ እና ዝኩል ቃና የተባሉ አካባቢዎች ተጠቃሾች ናቸው ።የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋንበሰሜን ሸዋ ደራ የተከሰተው ግጭት በተፋላሚዎቹ መካከል በአካባቢው እየተካሄደ ያለው ውግያ ሳምንት ሳምንት ሊሞላው ሲቃረብ በተለይ በዙሪያዋ ብርቱ ውግያ እየተደረገባት ከነበረችው ፈረስ ቤት ከተማ ነዋሪው ለደህንነቱ ሽሽት መግባቱን ዶይቼ ቬለ ከነዋሪዎች ጠይቆ ተረድቷል። የመከላከያ ሰራዊትም ወደ ፈረስ ቤት መቃረቡ ተሰምቷል። በክልሉ ከምዕራብ ጎጃም  በተጨማሪ ሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ አካባቢ እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት አካባቢዎች አለመረጋጋት መኖሩን ዶይቼ ቬለ ከየአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቆ ተረድቷል። በአማራ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ እና በክልሉ የጸጥታ ዘርፍ የተደረገው ሹም ሽር።በክልሉ ከከተሞች ውጭ ራቅ ብለው በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች ስልክ ሊሰራ ባለመቻሉ ዶይቼ ቬለ በወቅቱ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ጠይቆ ማወቅ አልቻለም ። በሌላ በኩል ግን አለመረጋጋት ይታይባቸው በነበሩ እንደ ደብረማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር እና አዴት ያሉ ከተሞች አንጻራዊ መረጋጋት እየታየባቸው እንደሚገኝ  ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በክልሉ ወደ መረጋጋት ከመጡ ከተሞች መካከል የባህርዳር ከተማ አንዷ ናት
በክልሉ አለመረጋጋት ይታይባቸው በነበሩ እንደ ደብረማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር እና አዴት ያሉ ከተሞች አንጻራዊ መረጋጋት እየታየባቸው እንደሚገኝ  ነዋሪዎች ገልጸዋል።ምስል Alemnew Mekonnen/DW
በአማራ ክልል ግጭት ጦርነቱን ሽሽት የተፈናቀሉ ዜጎች ተበራክተዋል
የመከላከያ ሰራዊትም ወደ ፈረስ ቤት መቃረቡ ተሰምቷል። በክልሉ ከምዕራብ ጎጃም  በተጨማሪ ሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ አካባቢ እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት አካባቢዎች አለመረጋጋት መኖሩን ዶይቼ ቬለ ከየአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቆ ተረድቷል።ምስል Alemnew Mekonen/DW

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ 

ኂሩት መለሰ