የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ
ረቡዕ፣ የካቲት 27 2011ማስታወቂያ
የአማራ ክልል ምክር ቤት 12 ተኛ መደበኛ ጉባኤ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ንግግር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። ምክር ቤቱ በዚህ ጉባኤ በክልሉ ሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በዝግ እየተወያየ መሆኑ ተነግሯል። አንድ የምክር ቤት አባል ለDW እንደተናገሩት ጉባኤው እየተወያየባቸው ካሉ ጉዳዮች መካከል ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ውዝግብ መፍታት የሚቻልበት መንገድ ይገኝበታል። ትናንት ደግሞ የምክር ቤቱ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የሰላም እጦት ላይ ባተኮረ ጽሑፍ ላይ በቡድን መወያየታቸውን የባሕር ዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ዘግቧል።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ