የመምሕራን ሠልፍ
ዓርብ፣ ግንቦት 23 2011ማስታወቂያ
የአማራ መስተዳድር መምሕራን ጥቅምና መብታቸዉ እንዲከበር፣ የትምሕርት ጥራት እንዲሻሻልና በተለያዩ አካባቢዎች የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንዲቆሙ ዛሬ ባደባባይ ሠልፍ ጠየቁ።የክልሉ መምሕራን ማሕበር በጠራዉ ሠልፍ የክልሉን ርዕሠ ከተማ የባሕርዳርን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች መምሕራን በየአካባቢያቸዉ ተሰልፈዉ አርፍደዋል።የማሕበሩ መሪዎች እንዳስታወቁት በሰልፉ የመምሕራን ኮሎጆች፣የቴክንኒክና የሙያ ትምሕርት ቤቶች፣ በየደረጃዉ የሚገኙ የአጠቃላይ ትምሕር ቤቶች መምሕራን በየሰልፉ ተካፍለዋል።የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን እንደዘገበዉ ባሕርዳር አደባባይ የወጡት መምሕራን በሺሕ ይቆጠራሉ።የአማራ ርዕሠ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት ኃላፊ የመምሕራኑን ጥያቄ በየደረጃዉ ላሉ የመንግስት ሹማምንታት ለማቅረብ ቃል ገብተዋል።
አለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ