የአለም የምግብ ቀን በሮማ
ሰኞ፣ ጥቅምት 6 2004ማስታወቂያ
የጀርመን ግብርና ሚንስትር -ኢልዘ አይግነርም- ከጉባኤው ተካፋይ አንዷ ናቸው። ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ እንደሆነ፤ በጉባኤው ላይ እንደሚያሳስቡ ለዶይቸ ቬለ ጀርመንኛው ክፍል ገልፀዋል። በማደግ እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ባለፉት አመታት ብቻ ከ 50 እስከ 80 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለውጭ አገር ባለሀብቶች ሰጥተዋል። በሌላ በኩል በአለም ዙሪያ 925 ሚሊዮን ህዝብ በርሀብ እንደሚሰቃዩ የአለም የምግብና የግብርና ድርጅት ገልፀዋል። የኢዛ አይግነርን ቃለ መጠይቅ ከዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ