የናይጀሪያ እና የአሜሪካ ግንኙነት
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 23 2010ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ከኾኑበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ኋይት ሐውስ ቤተመንግሥት ውስጥ የአፍሪቃ መሪን ተቀብለው ፊት ለፊት አነጋግረዋል። በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት አቀባበል የተደረገላቸው የናይጀሪያው መሪ ሞሐማዱ ቦሃሪ ናቸው። ሁለቱ መሪዎች በምጣኔ ሐብት እና ናይጀሪያን በሚያመሳቅለው የጸጥታ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ «እንኳን ደስ ያላችሁ» የሚል መግለጫቸ ከሰጧቸው በአፍሪቃ የተመረጡ መሪዎች መካከል የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሞሐማዱ ቦሃሪ ይገኙበታል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ