የኒዠር ደለል ውዝግብና የመፍትሔ ሀሳቡ
ዓርብ፣ ጥር 26 1998ማስታወቂያ
በናይጀሪያ በነዳጅ ዘይት በበለፀገው የኒዠር ደለል የቀጠለውን የኃይል ተግባር በቸልታ ማለፍ አይገባም የሚሉ የሀገሬው ምሁራን ለውዝግቡ መፍትሔ ለማፈላለግ ይረዳል ያሉትን ሀሳብ አቅርበዋል። በዚሁ ሀሳብ መሠረት፡ ዓለም አቀፍ ተሰሚነት ባገኙት ዕውቁ ናይጀሪያዊ የኖቤል ሰላም ተሸላሚ ዎሌ ሾይንካ የተደገፉት ምሁራን አንድ መፍቀሬ ብሔራዊ ጉባዔ የሚሰኝ ድርጅት አቋቁመዋል። ጉባዔው የተለያዩት የናይጀሪያ ብሔረ ሰቦች ባንድነት በሰላም ሊኖሩ የሚችሉበት ጉዳይ ላይ የመወያየት ዓላማ ይዞ ተነሥቶዋል።