1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኑሮ ዉድነት በትግራይ

ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2014

መቀሌ ዉስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 5 ብር ይሸጥ የነበረዉ 50 ግራም ዳቦ (ፉርኖ) ሰሞኑን 8 ብር ገብቷል።የፉርኖ ዱቄት፣የጤፍ፣ የበርበሬና የመሰል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ማኮሮኒና ፓስታን የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ ላይ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ

https://p.dw.com/p/4B90i
Äthiopien Mekele Mutter in Bäckerei
ምስል Million/DW

የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ነዉ

 

በጦርነት እና እገዳ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል በተገለለችዉ ትግራይ አለቅጥ የናረዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ የሕዝቡን ኑሮ እያቃወሰዉ መሆኑ ተዘገበ።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስሳሌ እንደዘገበዉ መቀሌ ዉስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 5 ብር ይሸጥ የነበረዉ 50 ግራም ዳቦ (ፉርኖ) ሰሞኑን 8 ብር ገብቷል።የፉርኖ ዱቄት፣የጤፍ፣ የበርበሬና የመሰል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ማኮሮኒና ፓስታን የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ ላይ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ።የዚያኑ ያክል እዚያዉ ትግራይ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉ ማጣፈጫዎች ዋጋ ብዙ ለዉጥ አላሳየም።የከብትና የስጋ ዋጋ ግን ቀንሷል።

ሚሊዮን ኃይለ ስሳሌ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ