የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን ለመታደግ የጋራ ፕሮጀክት
ሰኞ፣ ጥር 24 2013ማስታወቂያ
ህልውናው በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክን ለመታደግ ያስችላል የተባለ የጋራ ፕሮጀክት ስምምነት ይፋ ተደረገ ።ትናንት አርባ ምንጭ ላይ ይፋ የተደረገውን ፕሮጀክት በፌደራል መንግስት፣ በደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ 48 ባለድርሻ አካላት በስምምነት አጽድቀውታል።በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ገቢራዊ ይሆናል የተባለው ፕሮጀክት አሁን ፓርኩ የተጋረጠበትን ህገ ወጥ ሰፈራ ፣ የወሰን መካለልና ከተፈጥሮ ሀብት መመናመን ጋር በተያያዘ ያሉበትን ችግሮች ይቀርፋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ