የነዳጅ ፍሰትና ብክለት በአሜሪካ
ረቡዕ፣ ሰኔ 9 2002ማስታወቂያ
ፕሬዝዳንት ኦባማ ከሜክሲኮ ባሕር የሚፈልቀው ነዳጅ በተፈጥሮ ሐብት ላይ ያደረሰውን ብክለት ለመከላከል መስተዳድራቸው ስለሚያደርገው ጥረት ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ነዳጅ ዘይት በርካሽ የሚወጣና የሚገዛበት ዘመን አልፏል ፤ የብሪታኒያው የነዳጅ ዘይት ኩባንያ BP ካባሕር በታች ነዳጅ የሚያወጣበት ቧንቧ እና ጉድጓዶች በመፈንዳታቸው የሚፈሰው ነዳጅ አካባቢውን እየበከለ ነው ። ፕሬዝዳንት ኦባማ ብክለቱን ለመከላከል ረዥም ጊዜ ይጠይቃል ብለዋል ።
ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ