የትንሳኤ ዕለት ተቃዉሞ ሰልፍ
ሰኞ፣ መጋቢት 23 2005ማስታወቂያ
ሲቪሉ ኅብረተሰብ በብዛት የሚሳተፍበትና ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚያነሳዉ የትንሳኤ ዕለት ተቃዉሞ ሰልፍ ዘንድሮም ከዕለተ ዓርብ ማለትም የስቅለት ቀን አንስቶ እስከትንሳኤ ማግስት ማለት ማዕዶት ቀን ድረስ ኅብረተሰቡን የሚያሳስቡ ጉዳዮች ተነስተዉ ለፖለቲከኞች መልዕክት ይተላለፋል። በዘንድሮዉ የትንሳኤ በዓላቸዉ ጀርመኖች አራት አበይት ያሏቸዉን ጉዳዮች አንስተዉ ከዓርብ ዕለት ጀምረዉ በተለያዩ ከተሞች ተቃዉሞ አሰምተዋል። የተቃዉሞ ሰልፉ ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀስባቸዉ አካባቢዎች በተለያዩ ሁኔታዎች የሚከናወን እንደመሆኑ የተነሱ ነጥቦችን እንዲያጋራን የበርሊን ወኪላችንን ይልማ ኃይለሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ