የተባባሰው የሶማሊያ ውጊያ
ረቡዕ፣ ግንቦት 5 2001ማስታወቂያ
በዚሁ ውጊያም ከመቶ በላይ ሰዎች ተገድለዋል ፤ ወደ ሶሶት መቶ የሚጠጉ ቆስለዋል ፣ሀያ ሰባት ሺህ የሚደርሱ ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል ። ከአካባቢው በሚወጡ ዘገባዎች መሰረት መዲናይቱን መቅዲሾን ለመያዝ የሚዋጋው አልሸባብ በአሁኑ ጊዜ አብዛኛውን የከተማይቱን ክፍል ተቆጣጥሯል ። ባለፉት ሰባት ቀናት በሶማሊያ ተባብሶ ሰለቀጠለው ውጊያ ሂሩት መለሰ ሶማሊያዊውን ጋዜጠኛ ሙስጠፋ አብዲ ኑርን አነጋግራ ተከታዪን ዘገባ አጠናቅራለች ። ።
ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ