የተባባሰዉ የዩክሬን ቀዉስ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2006ማስታወቂያ
ሰዎች ሞተዋል ሄሊኮፕተሮች ወድቀዋል፤ ዘማች ወታደሮች ተንቀሳቅሰዉ የዜና ወኪሎች እንደሚሉት በገዛ ዜጎቻቸዉ ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ይህ ሁኔታም የአዉሮጳ መንግስታትን እያሳሰበ ይገኛል። ሩሲያ ዝም ብዬ አላይም ብላ በዩክሬን ላይ ዝታለች። በዲፕሎማሲዉ መንገድ መፍትሄ መፈለጉ አማራጭ የሌለዉ ነዉ ብለዉ የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በርሊን ላይ ድምፃቸዉን ማሰማታቸዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል በላከልን ዘገባ ጠቅሷል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ