ውይይት፦ የተባባሰዉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 15 2010ማስታወቂያ
መንግሥት ለሕዝቡ መሠረታዊ ጥያቄዎች ተገቢዉን መልስ አለመስጠቱ አለመረጋጋቱን እያባባሰ እንደሆነም ያመለክታሉ። የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባዉን በማካሄድ ላይ የሚገኘዉ ገዢዉ ፓርቲ ለዚህ ችግር መንስኤዉ የአመራር ድክመቱ መሆኑን ገልጿል። ሀገሪቱም አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለችም አመልክቷል። አንዳንዶች መንግሥት ይህን ይበል እንጂ ለሚታየዉ ችግር ፍቱን መፍትሄ ያመጣል የሚል እምነት እንደሌላቸዉ ይናገራሉ። በአንፃሩ ሌሎቹ ገዢዉ ፓርቲ ራሱን የመፍትሄዉ አካል ለማድረግ ፈቃደኝነቱ ካለዉ ጊዜዉ ቢረፍድም እንኳን እንደሚችል እምነት አላቸዉ። ዋናዉ ጥያቄ ግን አሁን የሀገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ እና የአለመረጋጋቱ ጉዳይ አቅጣጫዉ ወዴት እያመራ ነዉ? የሚለዉ ነዉ።
ሸዋዬ ለገሠ