የተባበሩት መንግሥታት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 1 2002ማስታወቂያ
ዋና ፀሐፊዉ ትናንት ዋሽንግተን ዉስጥ ሥለ ሴቶችና ሕፃናት ችግሮች ለመከረዉ ስብሰባ እንደነገሩት ድርጅታቸዉ የነደፈዉ የዓመአቱ ግብ ገቢር እንዲሆን አለም አቀፉ ማሕበረሰብ እስካሁን ከተደረገዉ ጥረት በላይ መጣር አለበት።በዚሁ ስብሰባ የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ድርጅት የሴቶችና የሕፃናትን ጤና ለማስጠበቅ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ባለቤቶቹ ቃል ገብተዋል።እርዳታዉ ከሚሰጣቸዉ ሐገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።ልደት አበበ ጉዳዩ የሚለከታቸዉን ሁለት የኢትዮጵያ መስሪያ ቤቶች ተወካዮችን አነጋግራለች።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ