የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ
ዕሁድ ዕለት በአዲስ አበባ ስለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ
ሰላማዊ ሰልፍ
አዘጋጆቹ ባቀዱት መሰረት ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ማካሄድ ባይችሉም፤ በአጠቃላይ የተካሄደው ሰልፍ በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የሰልፉ አዘጋጆች አስታውቀዋል።
የፍትህ ጥያቄ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 32ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ዕሁድ ዕለት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
የሰልፉ ቦታ
ሰልፉ ፓርቲዎቹ ባቀዱት መሰረት በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ አልቻለም። ከመንግስት ጋ ብዙ ድርድሮች ቢካሄዱም በመጨረሻ የሰልፉ አዘጋጆች የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና ሰልፉን ለማካሄድ መወሰናቸውን አሳውቀዋል።
የፖሊስ መመሪያ
ሰልፈኞቹ ወደ መስቀል አደባባይ መንገድ ሲጀምሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባልደረቦች የሰንሰለት አጥር ሰርተው መንገዱን ዘግተዋል። ፖሊስ ሰልፈኞቹን በድምፅ ማጉያ ሰልፉን ማድረግ ወደ ተፈቀደላቸው ወደ ጃልሜዳ እንዲሄዱ አሳስቧል።
መፈክሮች
የህዝቡ የመሬት ባለቤትነት ይረጋገጥ! የፀረ ሽብር ህጉ ይሰረዝ! የኢሀዲግ መገለጫው ሙስና ነው! የታሰሩ የህሊና እስረኞች ይፈቱ! የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችም ተሰምተዋል።
የጋራ ሰልፍ
ከዚህ ቀደም ተቃዋሚ ሰልፈኞች ተቃውሟቸውን በተናጥል ነበር የሚያሰሙት። አንድነት በጠራው የዕሁዱ ሰልፍ ላይ ግን የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች እና የፓርቲ ደጋፊዎች ተገኝተዋል። ይህ ሰልፍ በአይነቱ የመጀመሪያው ነው። የተለያዩ የፓርቲ ተወካዮችም በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ንግግር አድርገዋል።
የህሊና እስረኞች
ሰልፈኞቹ ፍትሃዊነት በጎደለው አሰራር ታስረዋል ያሏቸውን ፖለቲከኞች፣የሐይማኖት መሪዎች እና ጋዜጤኞችን ለማስታወስ ሞክሯል።
የአቶ ግርማ ጋዜጣዊ መግለጫ
አቶ ግርማ ሰይፉ- በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ተመራጭና የአንድነት የዲሞክራሲ እና ለፍትኅ ፓርቲ ከፍተኛ የአሰራር አባል ፤ዶይቸ ቬለን ጨምሮ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል።
የሰልፈኞች ጥሪ
የታሰሩ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲለቀቁ በዚህ ሰልፍ ላይ ጥሪ ተደርጓል። አሸባሪዎች አይደሉም የሚሉ መፈክሮችም ተሰምተዋል።
ሰላማዊ ትግል
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ሊቀመንበር -ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የሰልፉ ማሳረጊያ የሆነውን ንግግር አሰምተዋል። ሰላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።