የተቃዋሚ ፓርቲዎች ወቀሳና ምርጫ ቦርድ9 መጋቢት 2002ሐሙስ፣ መጋቢት 9 2002ኢትዮጵያ ዉስጥ በቅርቡ በሚደረገዉ ምርጫ የሚሳተፉ ተቃዋሚ ፓቲዎች በገዢዉ ፓርቲና በመንግሥት ባለሥልጣናት ይደርስብናል የሚሉትን በደል የሐገሪቱ ምርጫ ቦርድ እንደማይቀበለዉ አስታወቀ።https://p.dw.com/p/MW5Sምስል APማስታወቂያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎቻችን ይታሰራሉ፤ ይዋከባሉ በማለት ያማርራሉ። ምርጫ ቦርድ ግን ጉዳዩን አጣርቶ የተባለዉን ወቀሳ የሚያረጋግጥ መረጃ አለማግኘቱን አስታዉቋል። በሌላ በኩል ቦርዱ ሥለምርጫዉ ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች ጠጣር የሥነ-ምግባር ደንብ አዉጥቷል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለዉ። ታደሰ እንግዳዉ፤ ነጋሽ መሐመድ ሸዋዬ ለገሠ