የቦስተን አሸባሪዎችና የፖሊስ ክትትል ፣
ዓርብ፣ ሚያዝያ 11 2005
የሀገሪቱ ፌደራል የምርመራ ቢሮ FBI ትናንት በሰጠዉ መግለጫ ከሰኞ ዕለቱ የቦስተን ማራቶን ፍንዳታ ጋ በተያያዘ ሁለት ሰዎች መጠርጠራቸዉን ጠቁሟል። ከቅኝት ካሜራዎች የታየዉ ሌላኛዉ ነጭ የቤዝቦል ተጫዋች ኮፍያ እንዳደረገ የተገለፀዉ ተጠርጣሪ ግን አምልጧል። ተጠርጣሪዎቹ የቼቺንያ ዜጎች መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን ያመለጠዉ የ19 ዓመት ወጣት ቦስተን አቅራቢያ ካምብሪጅ ኗሪ እንደነበር አሶሲየትድ ፕረስ ዘግቧል። የቦስተን ፖሊስ ኮሚሽነር ኤድ ዳቪስ፤
«አሁን በመፈለግ ላይ የምንገኘዉ ተጠርጣሪ ቁጥር ሁለት በሚል የተገለፀዉን ሲሆን ባለነጭ ኮፍያዉ ግለሰብ በሰኞ ዕለቱ የቦስተን ማራቶን የቦምብ ጥቃት እጁ እንዳለ ይጠረጠራል።»
ከዚህም ሌላ ተጠርጣሪዎቹን በማደን ላይ ከነበሩ አንድ ፖሊስ መገደሉና አንድ ሌላ መቁሰሉም ተገልጿል። አያይዞም ፖሊስ የቦስተን ከተማ ኗሪዎች የሚታደነዉ ተጠርጣሪ አደገኛና መሳሪያ ሳይታጠቅ እንዳልቀረ በመግለፅ ከቤታቸዉ እንዳይወጡ አሳስቧል። ኗሪዎች በራቸዉን እንዲቆልፉና ለማያዉቁት ሰዉ እንዳይከፍቱም አስጠንቅቋል። የሰኞ ዕለቱ የቦምብ ጥቃት እስካሁን ለሶስት ሰዎች ህልፈተ ህይወት ምክንያት ሲሆን ቢያንስ አንድ መቶ ሰማንያ ሰዎችን ለጉዳት ዳርጓል። በጥቃቱ የተጎዱትን ለማሰብ ትናንት በቦስተን ከተማ ካቴድራል ዉስጥ በተካሄደዉ ስርዓት ላይ የተገኙት ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጥቃት አድራሾቹን አድኖ ለፍርድ ማቅረብ የማይቀር መሆኑን አመልክተዋል።
«ይህን ጥቃት ለፈፀሙትም ሆኑ ህዝባችንን ለመጉዳት የሚሞክር ማንም ቢሆን አዎ እናገኛችኋለን። አዎን ይዘን ለፍርድ እናቀርባችኋለን።»
ቦቦስተን ዓመታዊ የማራተን ውድድር የፈንጂ አደጋ ተጥሎ በዛ ያሉ ሰዎች ከቆሰሉና 3 ሰዎች ከሞቱ ወዲህ ፣ ፖሊስ ፣ አደጋ ጣዮችን በቪዲዮና በህዝብ እርዳታ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሌሊቱን ከፊል ውጤት ሳያስገኝለት አልቀረም፤ ከ 2 ቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንደኛው በአውቶሞቢል ለማምለጥ ሲጥር ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተገድሏል። ሌላው አልተያዘም ። መሣሪያ በመታጠቁም በህይወት ሊያዝ መቻሉ ሳያጠራጥር አልቀረም ። የቅርብ ጊዜ መጤዎች ናቸው ስለተባሉት 2 አሸባሪ የአሜሪካ ኑዋሪዎች ፣ የዋሽንግተን ዲ ሲ ውን ዘጋቢአችንን ፣ አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬው ነበር።
አበበ ፈለቀ
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ