1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ ስደተኞችን የማጓዝ ዕቅድ እና የፍርድ ቡት ውሳኔ

ሰኞ፣ ኅዳር 10 2016

ርታኒያ-ለንደን ባለፈው ዕሮብ ያስቻለው የአገሪቱ የይግባኝ ሰሚ ችሎት የጠቅላይ ሚኒስተር ሪሺ ሱናክ መንግስት ህገወጥ የሚላቸውን ስደተኖች ወደ ሩዋንዳ የማጋዝ ዕቅዱ፤ ህገወጥ መሆኑን በመግለጽ ቀደም ሲል በታችኛው ፍርድቤት የተወሰነውን ውሳኔ አጽድቆ እቅዱ ተግባራዊ እንዳይሆን አዟል።

https://p.dw.com/p/4ZE24
Frankreich-UK Migration | Vorfälle beim Überqueren des Ärmelkanals
ምስል Gareth Fuller/empics/picture alliance

የጠቅላይ ሚኒስተር ሪሺ ሱናክ መንግስት ከፍርድ ቤት የገጠመው ተግዳሮት

የብርታኒያ ፍርድ ቤት ውሳኔ

ብርታኒያ-ለንደን ባለፈው ዕሮብ ያስቻለው የአገሪቱ የይግባኝ ሰሚ  ችሎት የጠቅላይ ሚኒስተር ሪሺ ሱናክ መንግስት ህገወጥ የሚላቸውን ስደተኖች ወደ ሩዋንዳ  የማጋዝ ዕቅዱ፤ ህገወጥ መሆኑን በመግለጽ ቀደም ሲል በታችኛው ፍርድቤት የተወሰነውን ውሳኔ አጽድቆ እቅዱ ተግባራዊ  እንዳይሆን አዟል።

የብርታኒያና ሩዋንዳ ስምምነት

የብርታኒያ መንግስት  በተለይ በትንንሺ ጀልባዎች ባህር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኖችን  ወደ ሩዋንዳ በመላክ በዚያ በኩል እንዲስተናገዱ ለማድረግ ያሚስችል ስምምነት ከፉዋንዳ መንግስት ጋር መድረሱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህም  ሩዋንዳ የብርታኒያ መንግስት ጠርዞ የሚላካቸውን ስደተኖች የተገን ጥያቄ በመቀበል ውሳኔ እንድትሰጥ የሚጠይቅና ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኙ ስደተኖችም መኖሪይቸው እዚያው ሩዋንዳ እንጂ ብርታኒያ እንደማያሆን የሚደነግግ ነው።  ስምምነቱን፤  ስደተኖች በደረሱበት አገር የተገን ጥያቄ የማቅረብ መብታቸውን የሚነሳ፤ኢሰባዊና የዓለማቀፍ የሰብዊ መብት ድንግጊዎችን የሚጥስ መሆኑን በመግለጽ፤ በርካታ አገር በቀልና አለማቀፍ ድርጅቶች ቢያወግዙትም፤ የብርታኒያ መንግስት ግን ባለፈው አመት የመጀመሪያው ስደተኖችን የጫነው አውሮፕላን በረራ በአውሮፓ ፍርድር  ቤት እስክታገደበት ድረስ ገፍቶበት ነው የቆየው። ባለፈው ዕሮብ የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ብይን  ግን  መንግስት በታችኝው ፍርድ ቤት ውስኔ ላይ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ብርታኒያ የገቡ ስደተኖችን ወደ ሩዋንዳ መላክ ህገወጥ መሆኑን ያጸናበትና ተግብራዊነቱንም ያገደበት ነው።

በባህር አቆራርጠው እንግሊዝ የደረሱ ስደተኞች
የብርታኒያ መንግስት  በተለይ በትንንሺ ጀልባዎች ባህር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኖችን  ወደ ሩዋንዳ በመላክ በዚያ በኩል እንዲስተናገዱ ለማድረግ ያሚስችል ስምምነት ከፉዋንዳ መንግስት ጋር መድረሱ አይዘነጋም ምስል Daniel Leal/AFP/Getty Images

ፍርድ ቤቱ ስምምነቱን ውድቅ ያደረገባቸው ምክኒያቶች

ፍርድቤቱ በውሳኔው በሩውንዳ ያለውን የሰባዊ መብት  ይዞታና ተሞክሮ፤ የተቋማቱን ጥንካሬና ተአማኒነት፤ የፍርድቤቶቹን ነጻነትና ገለልተኝነት  መርምሮና አገናዝቦ፤ ስደተኖችን ወደ ሩዋንዳ መላክ መብታቸውን መጣስ ብቻ ሳይሆን፤ ለእደጋም ማገለጥ ሊሆን እንደሚችል አትቷል።፡በአምስቱም ዳኞች በሙሉ ድምጽ ያለፈውን ውሳኔ ፕሬዝዳንቱ ዳኛ ሮበርት ጆን ሪድ በንባብ ሲያሰሙ፤ ወደ ሩዋንዳ የሚላኩ ስደተኖች ሸሺተው ወደ መጡበት አገር ላለመላካቸው ዋስትና የሌለ መሆኑን ገልጸዋል፤ “ ወደ ሩዋንዳ የሚላኩ ስደተኖች ሸሺተውና አምልጠው ወደ መጡባቸው አገሮች ተጠርዘው ሌላኩ የሚችሉ መሆኑን የሚያሳዩ አሳማኝ ምክኒያቶች አሉ” በማለት ፍርድቤቱ በመንግስት ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ ያደረገው መሆኑን አስታውቀዋል።ትኩረት ለአፍሪቃውያን ስደተኞች

የብርታኒያ መንግስት ምላሽ

ውሳኔው ወደ ብርታኒያ የሚገቡ ስደተኖችን በእጅጉ ለመቀነስ ቃል ገብቶ ወደ ስልጣን ለመጣው የጠቅላይ ሚኒስተር ሱናክ መንግስትና ወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው ትልቅ ተግዳሮት ሁኗል። ሚስተር ሱናክ ከውሳኔው በኋላ በስጡት መግለጫ፤  የፍርድቤቱን ውሳኔ ቢይከብሩም፤  ለእቅዱ ተግብርዊነት ግን ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት፤ “ የተለየና አስቸኳይ ህግ በማውጣት ፓርላማው ሩዋንዳ ለስደተኖች ምቹ መሆኗን እንዲያረጋግጥ ይደረጋል” በማለት ማንም የውጭ ሀይል እቅዱ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚያስተጓጉልበትን ሁኔታ እንደሚታገሉ ገልጸዋል።

በባህር አቆራርጠው እንግኪዝ የደረሱ ስደተኞች
ውሳኔው ወደ ብርታኒያ የሚገቡ ስደተኖችን በእጅጉ ለመቀነስ ቃል ገብቶ ወደ ስልጣን ለመጣው የጠቅላይ ሚኒስተር ሱናክ መንግስትና ወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው ትልቅ ተግዳሮት ሁኗል።ምስል Gareth Fuller/PA/dpa/picture alliance

በአውሮፓ ህብረት የስደተኖች ፖሊሲ ላይ የሚኖረው እንደምታ

 ዕቅዱ የህግ መሰረት ያለውና ሌሎች አገሮችም በምሳሌነት እየወሰዱት መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል። “ የዚህን አይነት አሰራር ያቀድነው እኛ ብቻ አይደለንም። በአውሮፓ፤ ሌሎች አገሮችም ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰዱ ነው” በማለት ጣሊያን ጀርመንና ኦስትሪያ የነሱን ፈለግ እየተከተሉ መሆኑን አንስተዋል።፡ከሊቢያ ወደሩዋንዳ የተወሰዱ ስደተኞች

የውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱም በግል ወዳገሮቻቸው የሚገቡ ስደተኖችን ለመቆጣጠር ከሌሎች ሶስተኛ አገሮች ጋር የመስራትን አስፈላጊንት ቢያስታውቁም፤ እሳክሁን ግን ብርታኒያና ሩዋንዳ እንደገቡት አይነት ስደተኖችን ወደሌላ ሶስተኛ አገር የሚያስተላልፍ ስምምነት እንዳላደረጉ ነው የሚታወቀው። ጣሊያን በቅርቡ  ከባህር ላይ የምትታደጋቸውን ስደተኖች በአልባኒያ በማቆየት ጥያቄያቸውን ለማስተናገድ ከልባኒያ መንግስት ጋር የገባቸው ውል የሩዋንዳና ብርታኒያ ውል አይነት ባይሆንም፤ በራሱ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱበት ነው። ጀርመንና ለሎች አገሮችም በተመሳሳይ ሁኒታ ለተመሳሳይ አላማ ከሶስተ|ኛ አገሮች ጋር ለመስራት እያሰቡ ነው መባሉም፤ በህብረቱ አገሮች ዘንድ፤ በስደተኖች አጀንዳ ላይ ያለውን ልዩነት የበለጠ እንዳይሰፋውና የአውሮፓ ህብረት የጋራ የስደተኖች ፖሊሲ እውን መሆኛ ግዜም እንዳይርቅ የሚያሰጋ ሁኗል ።

ገበያውንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር