የብሪታኒያ ካሳ ለቀድሞ የዋንታናሞ ዕስረኞች8 ኅዳር 2003ረቡዕ፣ ኅዳር 8 2003የብሪታኒያ መንግስት ለቀድሞ የዋንታሞ ዕስረኞች ካሳ ለመክፈል መወሰኑን ትናንት አስታውቋል ። መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰውም በእስር ላይ ሳሉ በደል ደርሶብናል ሲሊ ከከሰሱ የቀድሞ እስረኞች ጠበቆች ጋር ለሳምንታት ከተካሄደ ድርድር በኃላ ነው ።https://p.dw.com/p/QBTDብንያም ሞሀመድምስል APማስታወቂያ ከፍርድ ቤት ውጭ በተካሄደ በዚሁ ስምምነት መሰረት መንግስት ለተበዳዮቹ ከ1 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም ከ 1.6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካሳ ይከፍላል ። ከፍተኛው ካሳ ከሚያገኙት ከሳሾች ውስጥ የብሪታኒያው ነዋሪ ኢትዮጵያዊው ብንያም ሞሀመድ አንዱ መሆኑን የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ዘግቧል ። ድልነሳ ጌታነህ ፣ ሂሩት መለሰ ሸዋዬ ለገሠ