የብሔር ብሔረሰብ ቀን ሲታሰብ
ዓርብ፣ ኅዳር 25 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች በትናንትናው ዕለት የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለ15ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡ኢትዮጵያ በመጣችበት ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ገደማ የብሔረሰቦች መብቶችን በማሻሻል በኩል ይበል የሚል ውጤት ብታስመዘግብም፤ ሂደቱ በሃገራዊ አንድነቱ ላይ ፈተናን ከመደቀኑ አልፎ በየአከባቢው ለሚነሱ የብሔር ግጭቶች ግን መፍትሄ ሊሰጥ እንዳልቻለ ይነገራል፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ሰብና ብዝሃነት አጥኚ የሆኑት ዶ/ር ኬሬዲን ተዘራ ለዶይቼ ቬለ አንዳሉት በኢትዮጵያ በብሔረሰብ ላይ የተዋቀረው ፌዴራላዊ ስርዓት ዋነኛ ተግዳሮቱ የብሔር ማንነቱን ከአገራዊ ማንነቱ ጋር እኩል ሚዛን አስጠብቆ አለመጓዙ ነው ይላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ወሊካችን ስዩም ጌቱ አነጋግሯቸዋል።
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ