የባን ኪሙን የሩዋንዳ ጉብኝት4 ጳጉሜን 2002ሐሙስ፣ ጳጉሜን 4 2002የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ባንኪሙን ሩዋንዳን ስላስቆጣው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በእንግሊዘኛው ምህፃር የ UNHCR ረቂቅ ዘገባ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር የጀመሩት ውይይት እንደሚቀጥል አስታወቁ ።https://p.dw.com/p/P7rOባን ኪሙንምስል APማስታወቂያ ትናንት ሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ውስጥ ከፕሬዝዳንት ካጋሜ ጋር የተነጋገሩት ባን እንዳሉት ፕሬዝዳንት ካጋሜ ውይይቱን ለመቀጠል ተስማምተዋል ። ባን በሰጡት መግለጫ ሩዋንዳ ፣ የዳርፉር የሰላም ተልዕኮዋን እንዳታቋርጥም ተማፅነዋል ። የሩዋንዳ መንግስት በበኩሉ ባን ኪሙን በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ኪጋሊ ድረስ በመምጣታቸው መርካቱን አስታውቋል ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ