የባራክ ኦባማ ዓመታዊ የመርህ ንግግር
ረቡዕ፣ ጥር 18 2003ማስታወቂያ
ፕሬዝዳንት ኦባማ በትናንትናው ምሽት ለሁለቱ ምክር ቤቶች ባሰሙት ዓመታዊ የመርህ ንግግራቸው ትኩረታቸው የአሜሪካንን ምጣኔ ሀብት ማሳደግ እዳዋን መቀነስና በትምሕርትና በሳይንስ ላይ መሆኑን አስረድተዋል ። በአሜሪካን የሚገኙ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች ጉዳይ እልባት እንዲያገኝም ጠይቀዋል ። በተለመደው የሪፐብሊካኖችና የዲሞክራቶች የአቀማመጥ ረድፍ ሳይሆን ተሰባጥረው በመቀመጥ ህብረታቸውን ላሳዩት የአሜሪካን የህዝብ እንደራሴዎች የህዝቡ ፍላጎት ጎን ለጎን መቀመጣቸው ብቻ ሳይሆን አብረው መስራታቸው መሆኑንን ተናግረዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ
ሽዋዬ ለገሰ