1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ከዓለም ስመ ጥር ባህር ኃይሎች አንዱ ነበር

ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2011

የባህር በር ከሌለ ባህር ሀይል ማቋቋም ቀልድ ነው

https://p.dw.com/p/395Ki
Helge Ingstad, norwegische Fregatte
ምስል Getty Images/AFP/A. Caballero-Reynolds

ሚሳኤል ወንጫፊ ጦር መርከቦች ነበሩን

"መልህቅ አርማዬ ቀይ ባህር ቤቴ 
ጀግንነት ውርሴ ያባት ያያቴ"


“ሚሳኤል ወንጫፊ ጦር መርከቦች ነበሩን። ትልቅ ባህር ሀይል ነው የነበረን።” ፒቲ ኦፊሰር ፍሬሰናይ ከበደ የባህር ሀይል ለማቋቋም የግድ የባህር በር ያስፈልጋል፤ የባህር ኃይሉም መፍረስ አልነበረበትም ይላሉ ፒቲ ኦፊሰር ፍሬሰናይ ከበደ። ለ18 ዓመት በቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሀይል አባል ሆነው አገልግለዋል። በአሁኑ ጊ ዜ ኑሯቸውን በእንግሊዝ አገር አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ከዓለም ስመ ጥር ባህር ኃይሎች አንዱ እንደነበር እና፣ እስከ ትልቁ የጦር ሚሳኤል ድረስ ታጥቆ ይንቀሳቀስ ነበር ሲሉ  ፒቲ ኦፊሰር ፍሬሰናይ እማኝነታቸውን ይሰጣሉ፡፡
የባህር በር ለሌላት ሀገር የባህር ኃይል ሠራዊት አስፈላጊ እንዳልሆነ ብዙዎች ቢናገሩም ፣ጠቃሚ ነው ሲሉ የሚከራከሩም አልጠፉም።  ፒቲ ኦፊሰር ፍሬሰናይ የባሀር በር ካለ ባህር ኃይል ያስፈልገናል በሚለው ሃሳብ ነው የሚስማሙት ። “ባህር ሀይል ለኢትዮጵያ አስፈላፊነቱ ወቅቱ እንደውም አልፏል። መፍረስም አልነበረበትም። የበሀር በርዋ ከተመለሰ ነው ታዲያ ባህር ሳይኖር ኢትዮጵያ የባህር ሀይል አላት ብሎ ማወጅ ፌዝ ነው። የግድ የባህር ሀይል መኖሩ መረጋገጥ አለበት።” የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የባህር ኃይል ሊኖረን ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል። ከ27 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ የባህር ኃይል ሰራዊት ልትገነባ ነው። ባህር ኃይሉ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ የሚያስችሉ ስራዎች በያዝነው ዓመት ተግባራዊ እንደሚደሚደረጉም ተሰምቷል። ኢትዮጵያ በንግድ መርከቦቿ ሸቀጥ ስታጓጉዝበት በቆየችው ቀይ ባህር፤ የባህር ኃይል ሰራዊቷን ነፍስ ልትዘራበት አቅዳለች። ሀገሪቱ አሁን ባላት የኢኮኖሚ አቅም እንዴት ባህር ኃይል ልታዋቅር ትችላለች ሌላው አንኳር ጥያቄ ነው። “ያደጉ አገራት ሳይቀሩ የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ለማቋቋም ትልቅ እርዳታ እንደሚያደርጉ አልጠራጠርም። ኢኮኖሚዋም ይፈቅዳል የሚረዱንም አገሮች ይኖራሉ።”
ካፕቴን ይገዙ ጋሻው በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ በሁለተኛ መኮንንነት እንዲሁም በውጭ ሀገር በካፕቴንነት ለ18 ዓመታት ሰርተዋል። በአሁኑ ጊዜ የመርከብ ትራንስፖርት ትምህርታቸውን በሆላንድ እየተከታተሉ እንደሆነ ነግረውናል። ባህር ኃይልን ሌላ ሀገር መመስረት ወታደራዊ ሚስጥርን ከመጠበቅ አንጻር ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን ይናገራሉ። የራስ ወደብ ሊኖር የሚችልበት መንገድ ቢቀየስ የባህር ሀይል በመዋቀሩ ይስማማሉ። “በመጀመሪያ የራሳችን ወደብ ያስፈልገናል። ከኤርትራም ጋር መደራደር ካለብን የተወሰነ መሬት በሊዝ ደረጃም ይሁን የራሳችን ወደብ ካለን ባህር ሀይል ማቋቋሙ ክፋት የለውም።” የሚገነባው የባህር ኃይል ጦር ሰፈር በቀይ ባህርና በህንድ ውቅያኖስ መካከል ከቀይ ባህር ዳርቻ ወደ ውስጥ 60 ኪሎ ሜትር ገብቶ በውሃው አካል ላይ ይሆናል ተብሏል።

Japan Flugzeugträger
ምስል picture alliance/AP Photo


ነጃት ኢብራሒም
ሂሩት መለሰ