ቢጫ ወባ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 11 2008ማስታወቂያ
የዓለም የጤና ድርጅት መንግሥታዊ ካልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የቢጫ ወባ ክትባት ዘመቻ ጀመረ። በዛሬዉ ዕለት በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ድንበር የለሽ ሃኪሞች፤ ሕፃናት አድን እና ሌሎች በርካታ ድርጅቶች ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር በመሆን 10,5 ሚሊየን የሚገመቱ ሰዎችን እስከ ቀጣይ አስር ቀናት ድረስ ለመከተብ ተሠማርተዋል። ክትባቱን በአንጎላ እና ኮንጎ ድንበር አካባቢም መስጠት ተጀምሯል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸዉ በሽታዉ ነአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ አስቀድሞ በመነሳቱ ወደ ኮንጎም እንዳይዛመት ለመከላከል ነዉ ክትባቱን የመስጠቱ ዘመቻ የተጀመረዉ። በዚህ ዘመቻም ከ 40 ሚሊየን በላይ ሕዝብ እንደሚከተብ ይጠበቃል።
ፀሐይ ጫኔ
ሸዋዬ ለገሠ