የቡድን ስምንት ጉባኤ
ሐሙስ፣ ግንቦት 18 2003ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ፤ ካናዳ፤ ብሪታንያ፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን፤ ጣሊያን፤ ጃፓን እና ሩሲያን ያካተተዉ ይህ ቡንድ በዚህ ወቅት ስብሰባዉ፤ በአረብ ሀገራት የተቀጣጠለዉን አብዮት እና በጃፓን ከባድ የመሬት ነዉጥ በፉኩሺማ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ላይ ያስከተለዉ አደጋ ላይ ትኩረቱን በማድረግ ይነጋገራል። የጉባኤዉ አስተናጋጅ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ለቱኒዚያና ለግብፅ የሚደረገዉን ድጋፍ እንደሚያጸድቁ ሲጠበቅ፤ ጉባኤዉ ከመጀመሩ አስቀድመዉ የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ቡድን ስምንት በሰሜን አፍሪቃ የምጣኔ ሃብት ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ