የቡድን ሰባት ጉባኤ ዉሳኔዎች
ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2007ማስታወቂያ
ምዕራባዉያኑ መንግሥታት ዐበይት የተባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተነጋገሩ ሲሆን በተለይ በመጪዉ ዓመት ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ ለሚካሄደዉ የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ የምስራች የሚሆን ዉሳኔ ማሳለፋቸዉ ተሰምቷል። መንግሥታቱ ከባቢ አየር ዉስጥ በመከማቸት የመሬትን የሙቀት መጠን እንዲጨምር አድርጓል የሚባለዉ የካርቦንን ልቀት የሚያስከትሉ የኃይል ምንጮችን የመቀነስ ዉሳኔያቸዉ በተግባር ከተገለጸም ታሪካዊ ርምጃ እንደሚሆን ነዉ ታዛቢዎች የሚናገሩት። ከዚህም ሌላ ጉባኤዉ በግሪክ የዕዳ ቀዉስ፤ በምሥራቅ ዩክሬን ብጥብጥና የሩሲያ ጣልቃ ገብነት፤ በስደተኞች መበራከትና በመሳሰሉት ላይም ተወያይተዉ ዉሳኔዎች አሳልፈዋል። ስለኃያላኑ መንግሥታት ስብሰባና ዉሳኔ የበርሊን ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ