የቀይ መስቀል እርዳታ ጥሪ
ሰኞ፣ ጥር 9 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፣ኢትዮጵያውን የመታው ድርቅ የምግብ እጥረት ባስከተለባቸው በአፋርና በሶማሌና በምሥራቅ ሐረርጌ አካባቢዎች እርዳታ መስጠት መጀመሩን አስታወቀ ። የድርጅቱ ሃላፊ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት የመንግሥትም ሆነ የሌሎች በጎ አድራጊ ድርጅቶች አቅም እስከሚጠናከር ቀይ መስቀል በነዚህ አካባቢዎች ቀድሞ ለመድረስ በመወሰን አስቸኳይ እርዳታ እየሰጠ ነው ።
ማህበሩ በሃገሪቱ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አስቸኳይ እርዳታ ለመለገስ የሚፈልጉ እርዳታቸውን በባንኮች በስልክና በሌሎችም የመገናኛ አገልግሎቶች መስጠት እንደሚችሉም ጥሪ አስተላልፏል ። በጉዳዩ ላይ የማህበሩን ዋና ፀሃፊና የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ አነጋግሯል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ