የሻርሊ ኤብዶ ሁለተኛ ሕትመት
ረቡዕ፣ የካቲት 18 2007ማስታወቂያ
ባለፈዉ ታሕሳስ ማብቂያ አሸባሪዎች በከፈቱት ጥቃት ባልደረቦቹ የተገደሉበት የፈረንሳይ የምፀት ጋዜጣ ሻርሊ ኤብዶ ከጥቃቱ በኋላ ዛሬ ሁለተኛ እትሙን ለገበያ አቅርቧል።«ተመልሰናል» በሚል ርዕሥ ዛሬ ለገበያ የቀረበዉ ጋዜጣ የሐይማኖት መሪዎችን፤ የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፖለቲከኞንና የጂሐዲስት ተዋጊ ምሥልን ይዞ ነዉ የወጣዉ።የፓሪሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነሕ እንደተከታተለችዉ ዛሬ የታተመዉ ጋዜጣ ቁጥር ጥቃቱ በተፈፀመ በሳምንቱ ከታተመዉ ያነሰ ቢሆንም ከጥቃቱ በፊት ይታተም ከነበረዉ ጋር ሲነፃፃር ግን ከፍተኛ ነዉ።ሐይማኖትን በሥልክ አነጋግሬያት ነበር።
ሐይማኖት ጥሩነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ