የሶርያ ስደተኞች እና ዩኤስ አሜሪካ
ሐሙስ፣ ኅዳር 9 2008ማስታወቂያ
ቴድ ክሩዝ እና ጄብ ቡሽን የመሳሰሉ የሬፓብሊካን ፓርቲ የ 2016 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ተፎካካሪዎች ደግሞ የኦባማ አስተዳደር ለክርስቲያን ሶርያውያን ስደተኞች ብቻ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመግብያ ፈቃድ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል። የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር ግን ስደተኞቹ አስፈላጊውን የምርመራና ማጣሪያ መስፈርት አሟልተው ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ በመሆናቸው አሸባሪዎች ሰርገው ሊገቡ የሚችሉበት እድል የለም ይላል። አብዛኛውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ኮንግረስ ወንበር የተቆጣጠሩት የሬፓብሊካን ፓርቲ አባላት ስደተኞቹ ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ረቂቅ ህግ ለማጽደቅ ለዛሬ ቀጠሮ የያዙ ሲሆን ከዋይት ሀውስ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ፕሬዝዳንቱ ረቂቅ ህጉን ይቀለብሳሉ ተብሏል።
ናትናኤል ወልዴ
አርያም ተክሌ
አዜብ ታደሰ