የሶሪያ ዉጊያና አካባቢዉ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 24 2004ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት እየከፋ በመጣዉ በሶሪያ ዉጊያና መዘዙ ላይ በዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደረጃ ለመወያየት ባስቸኳይ እንዲሰበሰቡ ምክር ቤቱ ጠየቀ።የቱርክ፥ የሊባኖስና የዮርዳኖስ ባለሥልጣናት ደግሞ ጦርነቱን ሽሽት ወደየሐገራቸዉ ለተሰደዱና ለሚሰደዱ ሶሪያዉን ተጨማሪ ርዳታ ለመጠየቅ በጋራ መክረዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ በሶሪያዉ ጦርነት ከሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብ ተገድሏል፥ ከሁለት መቶ ሺሕ በላይ ተሰዷል፥ ሰወስት ሚሊዮን ተፈናቅሏል።የጂዳዉ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ እንደተከታተለዉ የሶሪያዉ ዉጊያና ግጭት ቴሕራን-ኢራን ዉስጥ የተጀመረዉን የገለልተኛ ሐገራት ንቅናቄ ጉባኤንም ተጫጭኖታል።ዝር ዝሩ እነሆ።
ነብዩ ሲራክ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ