የስደተኞች ታሪክን የሚያወሳዉ ቤተ-መዘክር
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2007ማስታወቂያ
የቤተ መዘክሩ ሃሳብ በቀድሞዉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ ተጠንስሶ እንደ ጎርጎረሳዊዉ አቆጣጠር በ2007 ዓ,ም ግንባታዉ ቢጠናቀቅም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩት ኒኮላ ሳርኮዚ ቤተመዘክሩን ለመመረቅም ሆነ ለመጎብኘት ፍላጎት ባለማሳደራቸዉ ምክንያት ይፋዊ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ሳይደረግለት ላለፉት ሰባት ዓመታት ለመዘግየት ተገዷል። ቤተ መዘክሩን መርቀዉ የከፈቱት ፕሬዚደንት ፍራንሶዋ ኦላንድ፤ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ስደተኞችን በተመለከተ ሰፊ ግዜ ሰጠዉ ባደረጉት ንግግር የዛሬይቱ ፈረንሳይ በመጤዎች መልካም ተግባር መገንባትዋን አፅኖት ሰጥተዉ ተናግረዋል። ፀረ-ስደተኛ ስሜት ያላቸዉን ፖለቲከኞችም አዉግዘዋል።
ሐይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ