የሴቶች የፖለቲካ አመራር የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 29 2013ማስታወቂያ
የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሴት አመራር አባላት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪነት የጋራ ምክር ቤት አቋቋሙ። ምክር ቤቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሴቶችን ተሳትፎ እና የመሪነት ሚና አጉልቶ ለማሳየት ፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሁሉም መስክ ለማረጋገጥ ይሠራል ተብሏል ።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሥራ ላይ እያለ ሌላ የሴት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት ማቋቋሙ ተገቢነት ላይ ጥያቄ ተነስቶበት ነበር። ሆኖም የሴቶችን ተሳትፎ የላቀ ለማድረግ አስፈላጊ ነው በሚል ምክር ቤቱ ተመስርቷል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የቢሮ እና ሌሎች ድጋፎችን ያደርግለታል ተብሏል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ