የሴት ልጅ ግርዛት በአፋር
ሰኞ፣ የካቲት 2 2001ማስታወቂያ
በምስራቅ አፍሪቃ ልዩ የባህል አምባ እንደሆነች የሚነገርላት ኢትዮጵያ፤ በበርካታ ጎጂ ልማዶችና ባህሎች ስትጠቃ ይስተዋላል። የሴት ልጅ ግርዛት በሀገሪቱ የዚሁ የጎጂ ባህል አንዱ ነፀብራቅ በመሆኑ፤ ሴቶች ብዙውን ግዜ ተጎጂዎች ናቸው። በተለይ ደግሞ የሴት ልጅ ግርዛት በከፋ ሁኔታ በሚከናወንበት የአፋር ክልል። የዛሬው ዝግጅታችን በአፋር ክልል የሴት ልጅ ግርዛት ከባህልና ከእምነት አንፃር ምን እንደምታ እንዳለው፣ የችግሩ ጥልቀት እስከምን እንደሚደርስ የሚያስቃኘን ይሆናል።