የሲዳማ ሴቶች የሲዳማ ህዝብ በክልል እንዲደራጅ ጠየቁ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2011ማስታወቂያ
በሰልፉ ላይ የተገኙት የከልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት ያለውን የክልል መዋቅር ጥያቂ ተፈዳሚ ለማድረግ ከጎናቸው በመሆን አስፈላጊውን ድጋፈ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። በተለይም የደቡብ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በበኩላቸው ህዝቡ ያቀርበው ጥያቂ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የጀመረውን ትግል የአካባቢውን ሰላም በመጠበቀ ጭምር እንዲያካሂድ ጠይቀዋል።
በደቡብ ክልል ከሲዳማ ጨምሮ በዞን መዋቅር በመተዳደር ላይ የሚገኙ አስራ አንድ ብሔረሰቦች ራሳቸውን በክልል ደረጃ ለማዋቀር የሚያስችላቸውን ጥያቂዎች ማቅረባቸው ይታወሳል። ክልሉን በገዢ ፓርቲነት የሚመራው የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቂ ደኢህዲን / የክልል መዋቅር ጥያቂዎቹን የህዝቦችን ትስስር በማይበጣጥስ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለኝን ጥናት እያካሂድኩ ነው ሲል በቅርቡ ማስታወቁ አይዘነጋም። የሰልፉን ሂደት የተከታተለው የሀዋሳው ዘጋቢያችን ተከታዩን ዘገባ አድርሶናል።
ሽዋንግዛው ወጋየሁ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ