የሰቆጣና የአካባቢው ኑዋሪዎች ስሞታ፣ 22 ሐምሌ 2005ሰኞ፣ ሐምሌ 22 2005ባለፈው ቅዳሜ፤ የሰቆጣና አካባቢዋ ኑዋሪዎች ከላሊበላ -ሰቆጣ እንደሚሠራ ቃል የተገባልን አስፋልት መንገድ ተግባራዊ ይሁን በማለት አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።https://p.dw.com/p/19Gjcምስል Hugh Turralማስታወቂያ በበጀት እጥረት ሳቢያ ዘንድሮ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንደማይሆን ተነገረን ያሉት የሰቆጣና አካባቢዋ ኑዋሪዎች ኀዘን እንደተሰማቸውም ነው የገለጡት። በተጠቀሰው አካባቢ ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ባለመኖሩ፤ ባለተሽከርካሪዎች ወደዚያ መግባት እንደማይፈልጉና ፤ ህዝቡም ለከፋ ችግር መጋለጡንም ነው ኑዋሪዎቹ የሚያስረዱት። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ተክሌ የኋላ አርያም ተክሌ