የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር መርሐ-ግብር እና IAEA
ሰኞ፣ ሰኔ 29 2001ማስታወቂያ
ደቡብ ኮሪያዊዉ ዲፕሎማት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊነታቸዉ ሊፀድቅ ሰወስት ቀን ሲቀረዉ ከአለም አቀፉ ድርጅት ጋር የምትወዛገበዉ፤ የደቡብ ኮሪያ፣ሥም፣ ድንበር፣ ሕዝብ፣ ተጋሪ ግን ቀንደኛ ጠላት የኒኩሌር ቦምብ ሞከረች።ጥቅምት 2006 (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።) ጃፓናዊዉ ዲፕሎማት ለአዉቶሚክ ሐይል ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ሐላፊነት በተመረጡ ማግሥት፣ ከባለሥልጣኑ ጋር የምትነታረከዉ፣ የጃፓን ጎረቤት፥ ግን ታሪካዊ ጠላት ሚሳዬሏን ታንደቀድቀዉ ገባች።ቅዳሜ።ሰሜን-ኮሪያ።አጋጣሚ-ወይስ ሌላ? ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ላፍታ አብረን እንጠይቅ።
dw,Aግnturen
ነጋሽ መሐመድ