1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የሰሜን ኢትዮጵያው ቀውስ፣ የሰላም ፍላጎትና ፈተናዎቹ»  

እሑድ፣ ነሐሴ 30 2013

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እየተባባሰና እየተስፋፋ ሄዷል።ህዝቡን ያስጨነቀው በርካታ እልቂትና ጥፋት ያስከተለው ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ለረሃብ የመዳረጉ ስጋት አይሏል።ከዚህ በተጨማሪ ከ7 ሺህ በላይ ትምሕርት ቤቶችን እንዳልነበሩ ያደረገው ውጊያ፣ በርካታ ተማሪዎችን ከትምሕርት ገበታቸው አፈናቅሏል።

https://p.dw.com/p/3zwYE
Tigray Konflikt | Äthiopien Eritrea Flüchtlinge
ምስል GIULIA PARAVICINI/REUTERS

«የሰሜን ኢትዮጵያው ቀውስ፣ የሰላም ፍላጎትና ፈተናዎቹ»  

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እየተባባሰና እየተስፋፋ ሄዷል። ህዝቡን ያስጨነቀው በርካታ እልቂትና ጥፋት ያስከተለው ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ለረሃብ የመዳረጉ ስጋት አይሏል።ከዚህ በተጨማሪ ከ7 ሺህ በላይ ትምሕርት ቤቶችን እንዳልነበሩ ያደረገው ውጊያ፣ በርካታ ተማሪዎችን ከትምሕርት ገበታቸው አፈናቅሏል፤መምህራንንም ያለ ስራ እንዲቀመጡ አድርጓል። ግጭቱን ለማስቆም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ቢሰማም የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ህወሓት  ቀውሱን በንግግር ለመፍታት ምን ያህል ዝግጁ ናቸው የሚለው አጠያያቂ ሆኖ ቀጥሏል። ሱዳን ሁለቱን ወገኖች ለማደራደር ያቀረበችውን ጥያቄ ኢትዮጵያ ለመቀበል እቸገራለሁ ስትል ውድቅ አድርጋለች።ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሓት ደግሞ ለኢትዮጵያ መንግሥት ይወግናል ያለውን  የአፍሪቃ ኅብረትን አሸማጋይነት አልቀበልም ብሏል።መሰል ቅድመ ሁኔታዎች ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለታሰቡ ጥረቶች ማነቆ መሆናቸው ይነገራል። ታዲያ ግጭቱን እንዴት በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይቻላል? የሰላምና የማሸማገል ጥረቶቹ ተግዳሮቶችስ ምንድን ናቸው? ማነው ማሸማገል የሚችለው ፣ ማሸማገል ያለበትስ ማነው?«የሰሜን ኢትዮጵያው ቀውስ፣ የሰላም ፍላጎትና ፈተናዎቹ» የዕለቱ የእንወያይ ዝግጅት ትኩረት ነው ።

ኂሩት መለሰ