የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከእጩነት መሠረዛቸው 16 የካቲት 2007ሰኞ፣ የካቲት 16 2007አዲስ አበባ ውስጥ ፣ በአዲስ ከተማ ፤ ወረዳ 5 ፣ መርካቶ አካባቢ ለመወዳደር ተመዝግበው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅኔር ይልቃል ጌትነት፤ በምርጫ ቦርድ ደንብ ከአጩነት መሠረዛቸው ተነገረ።https://p.dw.com/p/1EgAcምስል DWማስታወቂያ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ እንዳለው በቆዬው የምርጫ ሕግ ፣ በአንድ ጣቢያ ከ 12 በላይ ተወዳዳሪዎች ሲቀርቡ፣ ባለፈ ምርጫ የተወዳደሩ ስድስት ፓርቲዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንዲያልፉ ይደረጋል። ቀሪዎቹ ስድስቱ በዕጣ እንዲለዩ ይደረጋል። በመሆኑም ፣ ኢንጅኔሩ ፣ የመመረጥ መብቴ ተነፍጓል ማለታቸው ተጠቅሷል። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ተክሌ የኋላ ኂሩት መለሰ