1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩሲያ ምርጫና የፕሬዝዳንት የፑቲን አሸናፊነት

ሰኞ፣ መጋቢት 9 2016

በምርጫው ውጤትና በፑቲን ድል ላይ የቻይና፣ ኢራን ቤላሩስና ጥቂት የማይባሉ የላቲን አሜሪካ አገሮች መሪዎች ፈጥነው የደስታ መልእክት አስተላለፈዋል። ቀድሞውንም የምርጫውን ሂደት የተቹትና ፑቲንንም በአምባገንነት የሚወነጅሉት የአሜሪካና አውሮጳ መሪዎች ግን ውጤቱን ፕሬዝድንት ፑቲን ብቻቸውን ተወዳድረው ያሸነፉበት ቲያትር በማለት ተሳልቀውበታል።

https://p.dw.com/p/4drw3
ፑቲን ከድሉ በኋላ ንግግር ሲያደርጉ
ፑቲን ከድሉ በኋላ ንግግር ሲያደርጉምስል Maxim Shemetov/REUTERS

የፕሬዝዳንት ፑቲን አሸናፊነትና የምዕራባውያን አስተያየት

በሩሲያ ላለፉት ሶስት ቀናት በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሩዝዳንት ቩላድሚር ፑቲን የመራጩን ህዝብ 88 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸናፊ መሆናቸው ተገልጿል። ፕሬዝድንት ፑቲን  የምርጫ ውጤቱ በምርጫ አስፈጻሚው አካል ይፋ መሆኑን ተከትሎ ባሰሙት ንግግር፤ ውጤቱ ሀዝቡ በእሳቸውና አስተዳደራቸው ያለውን እምነት ያረጋገጠበት መሆኑን ገልጸዋል፤ “  ድምጽ  ውጤቱ በህዝቡ በኩል ያለውን አሜነታ የሚያሳይ ነው። ወደፊት በርክታ ስራዎች ይጠብቁናል።በእቅዳችን መሰረት በመስራት ሀላፊነታችንን እንወጣለን በማለት የመረጧቸውንና እምንት የጣሉባቸውን ያገራቸውን ህዝቦች አመስግነዋል።

የተላለፉ መለዕክቶችና ትችቶች

በምርጫው ውጤትና የፕሬዝዳንት ፑቲን ድል፤ የቻይና፣ ኢራን፤ ቤላሩስና ጥቂት የማይባሉ የላቲን አሜሪካ አገሮች መሪዎች ፈጥነው የደስታ መልክት አስተላለፈዋል። ቀድሞውንም የምርጫውን ሂደት ሲተቹና ፕሬዝዳንት ፑቲንንም በአምባገንነት የሚወነጅሉት የአሜሪካና አውሮፓ መሪዎች ግን ውጤቱን  ፕሬዝድንት  ፑቲን ብቻቸውን ተወዳድረው ያሸነፉበት ቲያትር በማለት ተሳልቀውበታል።
ከሩሲያ ጋር በጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን ፕሪዝዳንት  ሚስተር ዘለንስኪ በበኩላቸው፤ “ የሩሲያ አምባገነን ገዥ አዲስ የምርጫ ቲያትር እየሰራ ነው።፤ አሁንም ባለፉት አመታት ሲያደርግ እንድቆየው ሁሉ ስልጣኑን ለማረጋግጥና ለሁልግዜም በስልጣን ለመቆየ ት የሚስራው  ቲያትር መሆኑን ሁሉም ያውቀዋል” በማለት ምርጫው ፕሬዝድንት ፑቲን አገዛዛቸውንና የጦርነት ፖሊሲያቸውን ያስቀጠሉበት ተውኔት መሆኑን ገልጸዋል።የሩስያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት

የሩሲያ ምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ማነጻጸሪያ

ፕሬዝዳንት ፑቲን ግን ምርጫው ህዝቡ በነጻነትና በፈቃዱ የፈለገውን የመረጠበት፤ የዴሞክራሲ መብቱን በመጠቀምም ለመሪዎቹ ይሁንታውን የስጠበት ነው በማለት በሩሲያ ምርጫ ሂደት ላይ የሚቀርቡ ትችቶችን ውድቅ አድረገዋል። ከአንድ የአሜሪካ መገኛኛ ብዙሀን፤ በምርጫው ዴሞክርሲያዊነት ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልስም፤ “ ምርጫው ዴሞክራሲያ እንደነበረ ነው የማምነው፤ ይልቁንስ በእናንተ አገር የአስተዳደር ስርዓቱ በተፎካካሪ ፕሬዝዳንቱ ላይ ፍርድ ቤት ሳይቀር እያሳደረ ያለውን ተጾኖ ማስተዋል ትችላላችሁ። እኛ የዚያ አገር ፕሬዝዳንት ምርጫ የለንም ህዝቡ ከመረጠው ጋር ነው የምንሰራው፤  ግን በተፎካክሪ ፕረዝደንቱ ላይ የሚሰራው አለምን በሙሉ ያስገረመ ነው” በማለት የሩሲያን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ አይደለም ለማለት ማንም የሞራል ብቃት ሊኖረው እንደማይችል አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን በበይነ መረብ  ድምጽ ሲሰጡ
ፕሬዝዳንት ፑቲን በበይነ መረብ ድምጽ ሲሰጡ ምስል Mikhail Metzel/REUTERS


 ለረጅም አመታት በስልጣን የቆዩ የሩሲያ መሪ

የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት  የስለላ ድርጅት ኬጂፕ  አባል የነበሩት የ71 አመቱ አዛውንት ፕሬዝድንት ፑቲን፤ አሁን ለፕሬዝዳንትነት የተወድደሩትና ያሸነፉት ለአምስተኝ ግዜ ሲሆን፤ ለቀጣዮቹ  ስድስት አመታትም  በሩሲያ የስልጣን ማማ ላይ የሚያቆይቸው ነው።  ይህም ፕቱንን በሶቭየት ህብረት ታሪክ ለረጅም አመታት በስልጣን ላይ የቆዩትን ጆሴፍ ስታሊንን የሚበልጡ እንደሚያደርጋቸው  ነው የሚነገረው።ሞስኮን ከምዕራባውያን ያፋጠጠው የሩሲያ አራት ግዛቶች ግንጠላ

ተሳትፎና ተቃውሞ

ከሩሲያ 114 ሚሊዮን  መራጭ ህዝብ ውስጥ 74 ከመቶው እንደመረጠና ይህም ከፍተኛው የህዝብ ተሳትፎ እንደሆነ ተገልጿል።። በቅርቡ በእስር ላይ እንዳሉ የሞቱት የተቃዋሚው አሌክሲ ናቫንሊ ባላቤትና ደጋፊዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት፤ በርካቶች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ተቃውሟቸውን 
መግለጻቸውም ተዘግቧል።

የሩሲያ ምርጫ ቀድሞና ዘንድሮ

ቀድሞ የሞስኮ ዲደብሊው ዋና ተወካይ የነበረው ጁሪ ሬስቼቶ  እንደገለጸው፤  የዘንድሮው ምርጫ ከቀድሞውዎቹ ምርጫዎች ጋር ይመሳሰላል፤ ይለያልም ፤”  በአንድ በኩል ይህ ምርጫ ኧንደሌሎቹ የሩሲያ ምርጫዎች አልፎ አልፎ ችግሮች የታዩበትና አሸናፊው አስቀድሞ የታወቀበት ነው፡፤ በሌላ በኩል በጦርነት ውስጥ የሚካሄድ በመሆኑ ፈጹም የተለየ ነው በማለት ይህ ሁሉ ሩሲያኖች በፕሬዝድንት ፑቲን ቀጣዮቹ ስድስት እመትት ብዙ ተስፋ  እንዳያደርጉ ሊያደርጋቸው ይችላል ብሏል።

ህዝቡ በመጨረሻው የምርጫ ቀን ድምጽ ለመስጠት ሲጠባበቅ
ህዝቡ በመጨረሻው የምርጫ ቀን ድምጽ ለመስጠት ሲጠባበቅምስል Maxim Shemetov/REUTERS

ፑቲን ተመራጭ የሆኑባቸው ምክንያቶች

ህዝቡ ለፕሬዝዳንት ፑቲንን ለአምስተኝ ግዜ የመረጠበት ምክኒያት ከዩክሬን ጋር በቀጥታና ከምራባውያን ጋር በተዘዋዋሪ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት፤ የሩሲያን ደህንነት በሚያረጋግጥ ሁኔታ  ለመቋጨት ፕሬዝዳንት ፑቲንን ተመራጭ አድርጎ በመውሰዱና፤  የሩሲያ ኢክኖሚም ከአሜሪካና  መዕራባውያን እየተደረገበት ያለውን ማዕቀብ መቋቋቋም በመቻሉ ነው የሚሉ ታዛቢዎች፤; ውጤቱ ግን በጦርነቱ እንዲቀጥሉና ከምራባውያን አንጻር የሚከተሉትን አሉታዊ ፖሊስም እንዲገፉበት ሊያደርጋቸው ንደሚችል ይገልጻሉ። 
ገበያው ንጉሴ
ለዲደብሊው
ብራስልስ