የሠብአዊ መብት ዕለትና ኢትዮጵያዉን ሠልፈኞች
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 1 2003ማስታወቂያ
እዚሕ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ሠብአዊ መብት ያከብር ዘንድ የጀርመን መንግሥት ግፊት እንዲያደርግበት በርሊን ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ ጠይቀዋል። በጀርመን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ያስተባበረዉ ሠልፈኛ ጥያቄዉን ለጀርመን መራሒተ-መንግሥትና ለዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ፅሕፈት ቤቶች አቅርቧል። የሠልፉን ሒደት የተከታተለዉን የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤልንና ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዷን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ