የሠማያዊ ፓርቲ ዉዝግብ
ማክሰኞ፣ ጥር 10 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎች እርስ በርስ እየተወዛገቡ ነዉ። የፓርቲዉ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ የፓርቲዉን ደንብ ጥሰዋል ያላቸዉን አራት ባለሥልጣናት ከአባልነት አባርሯል። የፓርቲዉ የሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ባንፃሩ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴዉን ዉሳኔ ሕገ-ወጥ በማለት ዉሳኔዉን ሽሮታል። «ተባረሩ» ከተባሉት አንዱ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴዉን ዉሳኔ የፓርቲዉን ትግል ለማደናቀፍ ያለመ «የግለሠቦች ሴራ» በማለት አዉግዘዉታል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሠ