1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የሞጣ ፀጥታ አስከባሪዎች ታሰሩ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 22 2012

ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 5 የከተማይቱ የፀጥታ አስከባሪ ኃላፊዎች መታሰራቸዉን የምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ዐስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3VZ6T
Äthiopien Stadt Motta
ምስል Motta City Communication Office

ባለፈዉ ታኅሣሥ 10 ሞጣ ምሥራቅ ጎጃም ዉስጥ፣ መሳጂዶችን፣ የንግድ ተቋማት ሲቃጠሉና ቤተክርስቲያን ላይ ቃጠሎ ሲሞከር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 5 የከተማይቱ የፀጥታ አስከባሪ ኃላፊዎች መታሰራቸዉን የምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ዐስታወቀ። የተቃጠሉትን መሳጂዶችና የንግድ ድርጅቶች መልሶ ለመገንባት የተለያዩ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ እየሰጡ ነዉ። መሳጂዶቹንና የንግድ ድርጅቶቹን አቃጥለዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ 33 ሰዎች መያዛቸዉን  ፖሊስ ከዚሕ ቀደም ዐስታዉቆ ነበር። የመሳጂዶቹና የንግድ ተቋማቱ መቃጠል የአማራ መስተዳድር ቃጠሎዉን አለመከላከሉና  ወንጀለኞቹን ፈጥኖ አለመያዙ ያስቆጣቸዉ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ድርጊቱን ማዉገዛቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ