የምድር ነውጥ በኢጣልያ፣
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 2001በተለያዩ ጊዜያት፣ በእሳተ ገሞራ አማካኝነት ይተነፍሳል።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ እንኳ፣ በሰሜን አሜሪካ «ሪዳውት» የተሰኘው ፣ በአላስካ የሚገኘው እሳተ-ገሞራ ፈንድቶ ደመና መሰል ዐመድ 20 ኪሎሜትር ድረስ ወደ ሰማይ መትፋቱ የሚታውስ ነው።
ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ፣ በደቡብ ምዕራብ ኮሎምቢያ የሚገኘው ጋሌራስ የተሰኘው እሰተ-ገሞራ፣ አምና በጥር ወር ከፈነዳ ወዲህ እንደገና ባለፈው የካቲት ተመሳሳይ ሁኔታ ታይቶበታል። በቺሌ ፣ በኤኳዶርም፣ እሳተ-ገሞራ በየጊዜው እየፈነዳ ፣ ህዝብ ማሸበሩ አልቀረም። በሩቅ ምሥራቅ፣ በጃፓንምከአንድ ወር ገደማ በፊት አሳማ በተባለው ተራራ የሚገኘው እሳተ-ገሞራ መፈንዳቱ አይዘነጋም።
በዓለም ውስጥ በዛ ያሉ እሳተገሞራዎች ያሏት ኢንዶኔሺያም ፣ ህዝቧ፣ በዚህ የተፈጥሮ ክስተት የቱን ያህል ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ያውቃል። ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የአሳተ-ገሞራ ምልክት ከሚታይባቸው 16 ያህል ቦታዎች አንዱ ፣ በአፋር የሚገኘው ኤርታሌ እሳተ-ገሞራ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት አልፎ- አልፎ አሥፈሪነቱን ያሥመሰከረ ሲሆን በዚያው በአፋር ምድር፣ መሬቱን በመሰንጠቅ 6 ሜትር ገደማ ስፋት ያለው ጉድጓድ የፈጠረው እሳተ-ገሞራ፣ የታላቁን ስምጥ ሸለቆ የወደፊት ዕጣ-ፈንታ በተመለከተ ጠበብት ፣ ይኸው የአፍሪቃ ክፍል በውቅያኖስ ሊከፈል ይችላል በማለት መላ-ምት እንዲደረድሩ አብቅቷቸዋል።
በዓለም ውስጥ ፣ የአሳተ-ገሞራና የምድር ነውጥ አደጋ እጅግ ከሚያሠጋቸው አገሮች አንዷ ኢጣልያ ናት ። ማሥጋት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጊዜያት አደጋው ደርሶባታል። ከሰሞኑም፣ በመሃል ኢጣልያ የምትገኘው ተራራማ ከተማ፣ ላ ኪላ ፣ የዚሁ የምድር ነውጥ ሰለባ ሆናለች።
ተክሌ የኋላ፣
ነጋሽ መሐመድ፣