የምድር ነውጥና እሳተ-ገሞራ
ረቡዕ፣ ሰኔ 8 2003ያም ሆኖ ፤ እሳተ ገሞራና የምድር ነውጥ ምንድን ነው ግንኑነታቸው?
በአፍሪቃው ቀንድ ፤ ከ 150 ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈነዳ እሳተ-ገሞራ፣ በህዝብ ዘንድ ያስከተለውን ድንጋጤ ያደረሰውንም መለስተኛ የበረራ አገልግሎት ሳንክ መነሻ በማድረግ በሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራችን እንዳስሳለን ። ለጥንቅሩ ተክሌ የኋላ-
የምድራችን ቁጣ ከሰሞኑ አየል ያለ መስሏል። ከትናንት በስቲያ በምሥራቅ ኢንዶኔሺያ በሱላዌሲ ደሴት በሪሽተር መለኪያ፣ 6,9 ‚ በአሜሪካውያን ተመራማሪዎች ምዝገባ መሠረት 6,2 የደረሰ ኃይለኛ የምድር መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበረ። በዚያው ዕለት፤ ከ 4 ወራት በፊት ክፉኛ የተጎዳችውን የኒውዚላንድ ከተማ ክራይስትቸርችን እንደገና አርገፍግፏት እንደነበረ ታውቋል። በቺሌ፤ ከፑየሁ ኮርዶን ኮዬ ተራራ ባለፈው ሰሞን የፈነዳ እሳተ ገሞራ፤ በአርጀንቲና ፣ ቺሌ፤ ዑሩጓይ እና ፓራጓይ የአየር በረራ እክል ፈጥሮ እንደነበረ አይዘነጋም። ጭሱ ከደቡብ አሜሪካ አልፎ፤ እስከኒውዚላንድና አውስትሬሊያ በበረራ አገልግሎት ላይ ችግር አስከትሎ ነበር።
ከሜክሲኮም ፖፖ ካቴ ፔትል ከተሰኘው ተራራ ከ 12 ቀን ገደማ በፊት እሳተ ገሞራ ፈንድቶ እንደነበረ የሚታወስ ነው። ይኸው በደቡብና ሰሜን አሜሪካ ፤ እንዲሁም በእስያ ከሰሞኑ በተመሳሳይ ወቅት የተከሠተ የምድር ነውጥ አፍሪቃንም ዳስሷል። አፋር ውስጥ በደንከል በረሃ፤ ኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ባለፈው እሁድ ፤ እኩለ ሌሊት ገደማ ላይ ፤ ዱቢ ከተባለው ቦታ ምናልባትም ናብሮ ከተሰኘው ኮረብታ ፣ እሳተ ገሞራ ከመፈንዳቱ በፊት በዚያው ዕለት በተደጋጋሚ የምድር ነውጥ ማጋጠሙ፤ ከፍተኛውም በ ሪኽተር መለኪያ 5,7 ደርሶ እንደነበረ ተገልጿል። የምድር ነውጥና እሳተ ገሞራ ምን ዓይነት ግንኙነት ነው ያላቸው? በኢትዮጵያ የሥነ-ምድር ሳይንስ፤ የኅዋ ሳይንስና ሥነ ፈለክ ተቋም (Geophysics , Space Science and Astronomy)
መምህር፤ ተመራማሪና በአሁኑ ወቅት በተጨማሪ የተቋሙ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሽመልስ ፍስሐ---
(ድምፅ) ------------- (3,29)
ባለፈው እሁድ ሌሊት በደንከል በረሃ የፈነዳው እሳተ ገሞራ፤ በስተምዕራብ 233 ኪሎሜትር ራቅ ብላ የምትገኘውን መቐለን ፣ ከተጠቀሰው እሳተ ገሞራ ከፈነዳበት ቦታ በስተሰሜን 350 ኪሎሜትር ራቅ ብላ የምትገኘውን አሥመራንም ማስደንገጡ አልቀረም። ሰኞ ጧት ለህዝቡ አስደንጋጭ ሆኖ ስለተገኘው ክሥተት በመቐለ የሳባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ (ሼባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ)የሥራ አመራር (ማንጅመንት ) መምህር ፣ አቶ መንገሻ ሀብቱ ከዚያ ዕለት አንስቶ እስከዛሬ ያለውን ሁኔታ፣ የዐይን ምሥክር እንደመሆናቸው መጠን እንዲህ ገልጸውልናል።
(ድምፅ)--------------------
ኢትዮጵያ የምድር ነውጥ የሚታወቅም የማይታወቅም በብዛት የሚከሥትባት አገር ናት። በሄይቲ አምና በጥር ብርቱ የምድር ነውጥ አደጋ ከደረሰ በኋላ ያነጋገርናቸው በካሊፎርኒያ ዩናይትድ እስቴትስ የሚኖሩት ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴ ምን ብለውን እንደነበረ እናስታውሳችሁ።
የምድር ነውጥ አደጋ ሊያጋጥም በሚችላባቸው አካባቢዎች የሚኖር ህዝብ ታዲያ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ነው ማድረግ የሚኖርበት ? በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ጉዳይ ይሆናል ፤
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ